ለሶስተኛ ዙር ለ300 አዲስ ሰራተኞች በተለያዩ ሀገራዊና ተቋማዊ ርዕሰ ጉዳዮች በአፍሪካ አመራር ልሕቀት አካዳሚ የሚሰጠው ስልጠው ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 2/2017 ዓ.ም ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።







በስልጠናው ቦታ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉትና የስራ መመሪያ የሰጡት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ሰላማዊት ዳዊት እንዳሉት፣ ተቋማችን ከያዘው ግብ አንዱ ለማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሀገር ደህንነት ማስጠበቅ ነው ብለዋል። ይህም ወደ አገር የሚገባውና ከአገር የሚወጣው ሰው ትክክለኛነትን በማረጋገጥ፣ አገርን ከመጠበቅ አኳያ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል።
ዳይሬክተሯ አክለውም ተቋምን መገንባት የመንግስት ስርዓት ግንባታ አካል በመሆኑ ሰልጣኞች በ’እንችላለን’ መንፈስ መስራት ይኖርባችኋል ብለዋል። ስራችሁን በቅንጅት መስራት ይኖርባችኋል ያሉት ኋላፊዋ፣ ብቁ፣ ንቁ እና አገልጋይ በመሆን አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ተቋም በጋራ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
ሰልጣኞች ከአእምሮ፣ ከስብዕና፣ ከክህሎት ዝግጁነት ባሻገር ራስን ትጉ ለማድረግ ራሳችሁን ዝግጁ ማድረግ ይኖርባችኋል ያሉት ሀላፊዋ፣ በመልካም ስነ-ምግባርና በቀናነት ማገልገል እንዲሁም አስፈላጊ ዕውቀትና ክህሎት መያዝና ዝግጁ መሆን ከሰልጣኞች እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል ፡።
የተቋሙ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ እና የዜግነት አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ፣ በየዘርፋቸው ያሉትን ተግባራትና ተጨማሪ የስራ መመሪያ ለሰልጣኞች ሰጥተዋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
