ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ወደ ተቋሙ ለተቀላቀሉ 250 አዲስ ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ።

የኢሚግረ‍ኤሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በስልጠና ቦታው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ተቋማችን ከያዘው ግብ አንዱ ለማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከሀገር ደህንነት አኳያ ወደ አገር የሚገባውንና ከአገር የሚወጣውን  ሰው ትክክለኛነት በማረጋገጥ አገርን ከመጠበቅ አኳያ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል። 

አክለውም በዜግነት ዘርፍ የተጀመረው የኤሌክትሮኒክ ፖስፖርት አዲስ ቴክኖሎጂ ከነባሩ ሰራተኛ ጋር አዲስ የሰው ሀይል አጣምረን የምንጠቀምበት ይሆናል ብለዋል።

ሰልጣኞች ከአእምሮ፣ ከስብዕና፣ ከክህሎት ዝግጁነት ባሻገር ራስን ትጉ ለማድረግ ዝግጁ መሆን ይኖርባችኋል ያሉት ዳይሬክተሯ በመልካም ስነ-ምግባርና በቀናነት ማገልገል፣ አስፈላጊ ዕውቀትና ክህሎት መያዝና ዝግጁ መሆን ከሰልጣኞች እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

ሰልጣኞች ላነሱት ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የተቋሙ የኢሚግሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ በበኩላቸው ተቋምን መገንባት የሀገረ መንግስት ስርዓት ግንባታ አካል በመሆኑ ሰልጣኞች በእንችላለን መንፈስ መስራት ይኖርባችኋል ብለዋል። 

አክለውም ስራችንን በቅንጅት በመስራት ብቁ፣ ንቁ እና አገልጋይ በመሆን አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ተቋም በጋራ መፍጠር አለብን ብለዋል።

ለ250 አዲስ ሰራተኞች  በተለያዩ ተቋማዊ ርዕሰ ጉዳዬች የሚሰጠው ስልጠና ከሚያዝያ 14-18/2017 ዓ.ም ለ5 ቀናት እንደሚሰጥ ተገልፆል።

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133