በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዘጋጅነት የድንበር ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ላይ  የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተጀመረ።

አዳማ: ግንቦት 22/2017 ዓ.ም 

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች፣ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት የሆኑ የመንግስት መስሪያቤቶችና  አጋር አካለት የሆኑት ዓለም አቀፍ ድርጅት ተዎካዮች በተገኙበት የድንበር ስትራቴጂ ረቂቅ  ሰነድ ላይ ውይይት ተጀምረዋል።

የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ ሚካኤል እንዳለ እንደ ተቋም እየተተገበሩ ከሚገኙ የለውጥ አጀንዳዎች አንዱ ዘመናዊና ጊዜውን የዋጀ የድንበር አስተዳደር መተግበር እንደሆነ ገልፀው አዳዲስ ከሚከፈቱ 21 የየብስ አስተዳደር ኬላዎች በተጨማሪ ነባር ኬላዎችን ለማዘመን የዲዛይን ስራ እንደተጠናቀቀ ተናግረዋል።

በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊና ተደራሽ የድንበር አስተዳደር በመተግበር የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና የአጋር አካላት ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን ያብራሩት አቶ ሚካኤል እንዳለ አገር አቀፍ የድንበር አስተዳደር የሚመራበት ስትራቴጂ አስፈላጊ በመሆኑ የቀረበው ረቂቅ ላይ በመድረኩ የተገኙ ባለድርሻና አጋር አካለት የነቃ ተሳትፎና አስፈላጊ ግብአት እንዲሰጡ አደራ ብለዋል።

በመድረኩ ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ተወካይ አቶ ተስፋዬ ወየሳ እና በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የየብስ ድንበር አስተዳድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማይ የማነ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት  እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በቀረበው  የድንበር ረቂቅ ጽሑፍ ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133