አዲሱ ኢ-ፓስፖርት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26 ፣ 2018 በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ቢቂላ መዝገቡ የሚመራው የልዑካን ቡድን በክልሉ የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት የሚጀመርበትን ሂደት በተመለከተ ከክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሐሰን ጋራ ውይይት አድርጓል።

ፓስፖርትን ተደራሽ በማድረግ ላይ ትልቅ ስራ መሰራቱን በማንሳት ፥ በክልሉም አዲሱን ኢ-ፓስፖርትን ማስጀመር ሌላ አቅም መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል ።

ከሰው እጅ ንክኪ በፀዳ መልኩ በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ የህዝብን ፍላጎት ለማርካት እና አገልግሎት ፈላጊዎች ያለ እንግልት በአቅራቢያቸው መገልገል እንዲችሉ መስራቱም በውይይቱ ላይ ክቡር አቶ ቢቂላ
አብራርተዋል ።

በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ላይ ጭምር የኢ-ፓስፖርት ግልጋሎት ለመስጠት ጭምር እንደሚሰራ ያነሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ፥ በክልሉ የሚጀምረው ኢ-ፓስፖርት የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ የማስፋፋት እና የተቋሙን የለውጥ አድማስ የስራ ስኬት የአሰራር ሂደትን ጭምር ለማስረፅ ሌላ አቅም መሆኑን ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግሥት ለተቋሙ ስኬታማነትና ትብብር እና ድጋፍ እንደሚያደርግ በውይይቱ ወቅት ገልፀው የተናበበ አሰራር ወጥነት ያለው አገልግሎት ለሀገራዊ አድገት ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/