አዲስ አበባ፣ሚያዚያ፣04፣2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት የሚደረገው ሀገር አቀፍ የቤተሰብ ምዝገባ አሁናዊ ልምድን የሚዳስስ ጥናት የመጀመሪያ ዙር ቀረበ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት እና የአገልግሎቱ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የቀረበው የጥናት ሪፖርቱ።
ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዲሁም ምክንያታዊ የሆነ እቅድ ለማቀድ የሚያስችለውን የቤተሰብ ምዝገባ ስርአት ጥንካሬዎችና ድክመቶችን በጥናቱ ላይ ተገልጿል።
የጋራ የመመዝገብ አላማ አለመኖር ፣ የህግ ማዕቀፎችን ጠንቅቆ ያለማወቅ ፣የምዝገባ ሁኔታዎችና የመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች መለያየት እና የመረጃ ልውውጥ ክፍተት በጥናቱ የታዩ ድክመቶች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን እኚህን ክፍተቶች በቀጣይ በማረም የተሻለ የምዝገባ ምህዳር እንደሚፈጠር የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አቅጣጫ ስተዋል ።
ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም በሪፎርሙ የቤተሰብ ምዝገባን በአዋጅ እንዲካተት የማድረግ ስራዎች መሰራቱን አውስተው ጥናቱ የዛሬውን የቤተሰብ ምዝገባ ስርአት ለማዘመን እና የመረጃን ትክክለኛነት ለማወቅ የሚያስችለን ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
የቤተሰብ ምዝገባን ዲጂታላይዝ ለማድረግና አዲስ ሲስተም ለማስጀመር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የጥናቱ አካል እንዲሆኑም ጠይቀዋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ቢቂላ መዝገቡ ጥናቱ የቤተሰብ ምዝገባ ፅንሰ ሀሳብ ግንዛቤን በሰፊው መዳሰስ እንዳለበት በማንሳት የጥናት አካባቢዎች ልየታ የቦታ መረጣ የጥናቱን አላማን መሰረት እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡
ክቡር አቶ ቢቂላ አክለውም ይህ ጥናት መሰረታዊ የቤተሰብ ምዝገባ ችግሮችን በመለየት መደበኛ የቤተሰብ ምዝገባን ለማስጀመር ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑም አስገንዝበዋል፡፡
የግብአት ማሰባሰብና አውደ ጥናት ከተካሄደ በሗላ የመጀመሪያው የጥናት ውጤት በቀጣይ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
