ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊትን ጨምሮ ከፍተኛ የአገልግሎቱ የስራ ኃላፊዎች ተቋሙ እያከናወናቸዉ የሚገኙ የዲጅታላይዝሽን ስራዎችን ገምግመዋል።
በግምገማው ላይ በዋናነት በቅርቡ ወደ ስራ በሚገባዉ የወርቃማ መታወቂያ ካርድ (Golden ID card) በዉስጥ ሊካተቱ በሚገባቸዉ መረጃዎች እና ዲዛይን ፣ በአዲሱ የተቋሙ የፖርታል ሲስተም እንዲሁም ገቢና ወጪ መንገደኞችን በአሻራ ብቻ ማስተናገድ በሚያስችለዉ የ E-GATE አገልግሎት ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ሃሳቦች ቀርበዉ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
ተቋሙ በየጊዜዉ እያከናወናቸዉ የሚገኙ የዲጅታላይዝሽን ስራዎች የፓስፖርት፣ የቪዛ፣ የትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንዲሁም የቁጥጥር ስራዎችን ፍጥነት እና ጥራት በማሻሻል የደንበኞችን እርካታ እዉን በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በግምገማዉ ወቅት ገልጸዋል።
ወይዘሮ ሰላማዊት አያይዘዉም አዳዲስ የዲጂታላይዜሽን ስራዎች በቶሎ በማጠናቀቅ በፍጥነት ወደ ተግባር ሊገቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
