የኤርፖርት እና የድንበር አስተዳደር ስራን ማላቅ፥የሀገር ገፅታን መቀየር ነው ተባለ

ሰኔ ፣ 21 ፣ 2018 ዓ.ም የኤርፖርት እና የድንበር አስተዳደር ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም በሚል የውይይት ማዕቀፍ ላይ የምክክርና የግብአት ማሰባሰብ ወርክ-ሾፕ ከፍተኛ የክልል እና የፌዴራል ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተካሄዷል።

የኤርፖርት እና የድንበር ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘመን ያላትን ተወዳዳሪነት የምታረጋግጥበት ስትራቴጂካዊ ግብዓት ነው ሲሉ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አንስተዋል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት፤ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንደተናገሩት፤ ፕሮግራሙ እንደሀገር የሚያጋጥሙ የደህንነት ስጋቶችን በመረጃ አስደግፎ ለማወቅና ለመከላከል ጉልህ ሚና ያበረክታል ሲሉ አንስተዋል።

በጋራ የተቀናጀ ስራ መስራት ይኖርብናል ፣ የአየር ድንበር እና የየብስ አስተዳደርን ማላቅ ይገባል ፣ ድንበርን ማላቅ ዜጋን ከመጠበቅ በላይ ሁለተናዊ የብልፅግና ጉዞ ላይ ዋጋው የማይተመን ነው ያሉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ሰላማዊት ዳዊት የኢትዮጵያን ድንበር በአግባቡ መረዳት ለስራ መናበብ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

በቅንጅት ሆኖ ብሄራዊ ደህንነትን እና የሰዎች ነፃ ዝውውርን ከመልካም አስተዳደር ስራ ጋር በማያያዝ የእግድ ሂደትን ማዘመን ያስፈልጋል በማለት በዚህ እረገድ ወደ ኋላ በመመለስ ጭምር ሰነድ በማጣራት የሀገሪቱን የተቀናጀ የአየር የድንበር አስተዳደር ማከም ላይ በጋራ መስራት ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል ዋና ዳይሬክተሯ።

ሀገሪቱ የገጠማትን ችግሮች በቅንጅት ለመፍታት ቁልፍ መስኮች ላይ ፣ በግዜ የለንም መንፈስ መረባረባችን የኤርፖርት እና የድንበር አስተዳደር ስራን ማላቃችን ፥የሀገር ገፅታን መቀየር መሆኑ የፌዴራል ፓሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል አስገንዝበዋል።

ሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን በስፋት እንዲለሙ በማድረግ የሀገሪቱን የሳይበር ሉዓላዊነትና የጋራ የመረጃ ቋት በአንድነት በማስተዳደር ከአለም አቀፍ ኑባሬ መጓዝ ይገባል ብልዋል ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ።

ለፕሮግራሙን ውጤታማነት ከ10 ተቋማት የተውጣጡ ብሔራዊ አስተባባሪና ቴክኒካል ኮሚቴዎችን ያካተተ ዐቢይ ኮሚቴ ተቋቁሞ በዘመኑ ቴክኖሎጂ ታግዞ የቅንጅት ስራ ለመስራት ዝግጀት ማለቁም በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !

————————

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……

Telegram: https://t.me/ICS_EthiopiaFacebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopiaTwitter: https://twitter.com/ics_ethiopiaTikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopiaLinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopiaYouTube: https://www.youtube.com/@Ics_EthiopiaInstagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/