ሰኔ 14 ፣ 2018 ዓ.ም ባለፋት ጥቂት አመታት በተሰሩ ዘርፍ ብዙ ስራዎች ተቋሙ ከመዋቅራዊ ለውጦች እና ሽግግር ባሻገር ተምሳሌት መሆን የቻለበትን ጉዞ በሰራተኞች የዕለተ ተዕለት ትጋት ማረጋገጥ መቻሉን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ከመላ ሰራተኞች ጋር በነበራቸው የጋራ ውይይት መድረክ ላይ አንስተዋል።
በጋራ የሰራተኞች ውይይት ላይ የተገኙት ዋና ዳይሬክተሯ ኢትዮጵያን አሸናፊ በማድረግ ሂደት ላይ አገልግሎቱ የተወጣው ሃላፊነት ትልቅ መሆኑን በማንሳት፥በሰራተኞች ሙሉ ትጋት በአመቱ የተመዘገቡት ስኬቶች ልዩ ናቸው ብለዋል።
በአገልግሎት አሰጣጥ ፣ በሰራተኞች ስልጠና ፣ በቴክኖሎጂ ለውጥ እና እድገት ፣ የክልል ቅርንጫፍን በማስፋፋት ፣ ከአሮጌው ወደ አዲስ የስራ ምህዳር የተሸጋገረው ተቋሙ በጋራ ጥረት በመሆኑ በቀጣይም ሁሉም ባለድርሻ በዚህ የስራ ሃላፊነት እና ትጋት መቀጠል እንዳለበት ዋና ዳይሬክተሯ አስገንዝበዋል።
የአገልግሎቱ ማሸነፍ የሀገር ማሸነፍ ነው ትልቅ የድል ብስራተ መነሻ ጭምር ነው ተብሏል።
የመድረኩ ተሳታፊ ሰራተኞች የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
