ሰኔ 16 ፣ 2018 ዓ.ም የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ ይፋ በሆነው እስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም ቪዛ ዙሪያ ከቱሪዝም ሚንስቴር ፣ አየር መንገድ እና ኢንሳ ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄዷል።
በውይይቱ የቪዛ አሰራር ቴክኖሎጂ ልህቀትን በስራ ላይ ማዋል እና በቅንጅት በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
ከቱሪዝም ሚንስቴር ጋር በመተባበር የሚተገበረው አሰራሩ በሀገሪቱ የቱሪዝም አድገት ላይ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።
በውይይቱ ላይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬከተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ፣ የቱሪዝም ሚንስትር ሚንስቴር ዳኤታ የሆኑት ዶክተር እንዳገና አበበን ጨምሮ የአየር መንገድ እና የኢንሳ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
