አዲስ አበባ፡ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ/ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መርህ የሚከናወነው የዘንድሮውን 8ኛዉን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ማንጎ፣ አቮካዶን ጨምሮ ሌሎች ለምግብነት የሚዉሉ ችግኞችን በጎተራ ማሳለጫ በመትከል ተቀላቅለዋል።
የክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎች አንዱ የሆነውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን በይፋ ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የሆነውን የችግኝ ተከላ ስራ ለበርካታ አመታት ሲያከናውን መቆየቱን አስታዉሰዋል። በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተቋሙ ሃያ ስምንት ሺህ ችግኞችን ለመትከል ማቀዱም ተናግረዋል።
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንዲሁም በክልል ከተሞች በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዋና ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡
ችግኝ መትከል ባህል እየሆነ መምጣቱን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሯ ተቋሙ የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራዉንም አጠናክሮ በመቀጠል የሀገራችን የተፈጥሮ ገጽታ ከመገንባት ባሻገር የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋጽዖ እንደሚወጣ ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ የተገኙት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ብርሃኑ አበራ በሀገራችን የሚከናወኑ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች የአየር ንብረት ተፅእኖን በእጅጉ እያሻሻሉና የአዲስ አበባና የከተሞችን ገፅታ እየቀየሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
