የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ የዲጅታል ሲስተም ስራዎችን ገመገመ።

መጋቢት 25/2018 አ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እና የአገልግሎቱ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ የኦንላይን ፖርታል ሲስተም ጨምሮ ሌሎች የዲጂታል ሲስተም ስራዎችን ገምግመዋል።ግምገማው በአዲሱ የፖርታል ሲስተም ፥ ገቢና ወጪ መንገደኞችን በአሻራ ብቻ ማስተናገድ የሚያስችል የ E-GATE አገልግሎት እንዲሁም በቅርቡ በሚጀምረው የወርቃማ ቪዛ (Golden Viza) ሊኖረዉ በሚገባ ዲዛይን ዙሪያ ያተኮረ ነበር።

በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ የዲጅታላይዜሽን ስራዎች ተቋሙ አገልግሎት በሚሰጥባቸዉ በአዲስ አባበ እና ሌሎች የክልል ቅርንጫፎች፣ በውጭ ሀገራት በሚገኙ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች እንዲሁም በመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ፈጣን፣ ጥራት ያለዉ እና የተሻለ የፓስፖርት፣ የቪዛ፣ የትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ገልፀዋል።

አዳዲስ የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን በቶሎ በማጠናቀቅ ወደ ተግባር ሊገቡ እንደሚገባ ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !

————————

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……

Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia

Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia

Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia

TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia

LinkedIn:https://www.linkedin.com/company/icsethiopia

YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia

Instagram:https://www.instagram.com/icsethiopia/