የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ለአረጋዊያንና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርቷል !

አዲስ አበባ፡ ሚያዚያ 04/2018 ዓ.ም.

ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጉለሌ በሚገኘው ተስፋ ብርሃን ምግብ ማዕከል ለ500 መቶ አረጋዊያን አቅመ ደካማ ወገኖች የበዓል ድባብ ቤተሰባዊ ስሜት በሞላው ሁኔታ እንዲያከብሩ ለማስቻል የማዕድ ማጋራት አካሂዷል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የለዉጡ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በኢትዮጵያ የመረዳዳት ባህል ከፍ ብሏል ፤ ሁሉም በሚችለው ልክ አቅም በፈቀደ መልኩ ለህዝብ በመቆም ላይ ይገኛል ብለዋል። የዛሬው ተግባርም የመንግስትን ቋሚ ሰው ተኮር እሴት መሰረት ባደረገ መልኩ የተከናወነ መሆኑንና ለህዝቡ ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአልን በዚህ መልኩ በመረዳዳት ማሳለፍ የነበረውን ሀገራዊ እሴት ለማፅናት የሚረዳ ትልቅ ተግባር ነውም ነው ያሉት ወይዘሮ ሰላማዊት።

በበአሉን ላይ የተሳተፋ አረጋዊያን አቅመ ደካሞች በአሉን በዚህ መልኩ በማሳለፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ሌሎች ተቋማትም ይህን ምሳሌ በማድረግ የመረዳዳት ባህልን እና እሴትን ሊያስቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/