የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች  በሀገራዊ የ2017 ዓ.ም የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አደረጉ። 

ሚያዚያ 9/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሀገራዊ ለውጡ ያስገኛቸው ትሩፋቶችን አፅንቶ በማስቀጠል ለቀጣይ ተልዕኮ በየደረጃው ያለ አመራር ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል። 

የተቋሙ የዕቅድና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሳይ አበበ የሀገራዊ የ2017 ዓ.ም የ9ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ያቀረቡ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ እና  የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃጸም ላይ ሰራተኛው ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡ 

በመጨረሻም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ እና  አቶ ጎሳ ደምሴ በተነሱ ሀሳቦች ላይ  ማብራሪያ በመስጠትና የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡