የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት  አዲስ እየተሰራ ያለውን የኦንላይን ፖርታል ሲስተም ገመገመ።

አዲስ አበባ: 26/09/2017 ዓ.ም

ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የአገልግሎቱ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ቶፖን ኩባንያ እያበለፀገ ያለው አዲሱ  የዲጅታል ሲስተም ተገምግሟል። 

በግምገማው ወቅት አዲሱ ሲስተም ለተገልጋይ ምቹ እንዲሆን ግብአት የተሰጠ ሲሆን በግብአቱ መሰረት ማሻሻያ እንዲደረግበት  ተመላክቷል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እያከናወናቸው ካሉት የለውጥ አጀንዳዎች አንዱ ከዘመኑ ጋር የሚሄድ የዲጂታል ሲስተም ተግባራዊ ማድረግ ነው።

 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት