ሐዋሳ ፣ የካቲት 21 ፣ 2018 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ልኡካን ቡድን ከሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡሩ አቶ ደስታ ሊዳሞ ጋራ ከሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ጋራ በተያያዘ የአሰራር እና የስርአት ግንባታ ላይ ውይይት አድርጓል ።
የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ስረአት ግንባታን በህግ እና በቴክኖሎጂ በመምራት ማህበረሰብን በኢኮኖሚ ደረጃ መለየት እና ማጣራት የቤተሰብ ምዝገባ ላይ ከታችኛው መዋቅር ጀምሮ በቅንጅት መስራት ለጋራ ስኬት ወሳኝ ነው ያሉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ከሲዳማ ክልል ጋራ በቀጣይ በነዚህ ዘርፎች በቅንጅት እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።
የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባውን ማዘመን እና በመናበብ መስራት መረጃን ከመተንተን ባሻገር ለሀገራዊ የልማት እቅድ ግብአት ጭምር መሆነን ዋና ዳይሬክተሯ ገለፀው ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ላይ ትብብር የጋራ ቅንጅት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል ።
የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ደስታ ሊዳሞ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ላይ ክልሉ መሪ መሆኑን በማንሳት ፥ለስራው ስኬት ብዙ ክንውኖች ተሰርቷል ፣ የመረጃ ክፍተትን የሚሞላ ግልፅ ተልዕኮ ለመያዝ የሚረዳ ውይይት ነው ብለዋል ።
አክለውም ፕሬዚዳንቱ የዛሬው ውይይት ለሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባው የተሻለ ስራን በእንቅስቃሴ ለመተካት እሳቤውን በማህበረሰቡ ለማስረፅ እና አሰራሩ የተሻለ ይሆን ዘንድ አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።
ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንሰቲትዩት ጋራ በመተባበር ሁሉም በሚገባው ቋንቋ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባውን ማሳለጥ መቻሉ ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ግብአት የሚሆን መረጃ የሚስጥ መሆኑን የዜግነት ዘርፍ ሃላፊ እና የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ቢቂላ መዝገብ አንስተዋል
የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አድገት ለማጉላት እና የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን ማወቅ እና መተንተን ላይ ድርሻ እንዳለው ክቡር አቶ ቢቂላ መዝገቡ ገልፀው ይህ ውይይት ክልሉ በዚህ መልኩ መጓዝ እንዳለበት የጋራ መግባባት የሚፈጥር ነው ብለዋል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_EthiopiaFacebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopiaTwitter: https://twitter.com/ics_ethiopiaTikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopiaLinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopiaYouTube: https://www.youtube.com/@Ics_EthiopiaInstagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
