”የሴቶች ሁለተናዊ ተሳትፎ ለሀገራዊ የለውጥ ጉዞ አጋዥ ነው ” ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር

ሐዋሳ ፣ የካቲት ፣ 22 ፣ 2018 ዓ.ም የሴቶች ሁለተናዊ ተሳትፎ በሁሉም የስራ መስክ ላይ ለማጠናከር እና በሀገር ግንባታ ላይ ድርሻቸውን በላቀ ትጋት ይፈፅሙ ዘንድ የሚያስችል ስልጠና ማርች ኤይትን ምክንያት በማድረግ በሐዋሳ ከተማ እየተሰጠ ነው።

በስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት
ማርች ኤይት የሴቶችን ማንነት ፣ ማህበራዊ ሃላፊነት እና
ህይወት ላይ ያላቸውን አስተዋጽኦ የምናከብርበት ዕለት መሆኑን አንስተዋል።

ዕለቱ ልዩ ቀን ነው ፣ ሴት መሪ ናት ፣ እናት ናት ይህም በተፈጥሮ የተሰጣት ነው ይህን ተፈጥሮ እራስን በማብቃት መንከባከብ ይገባል በማለት ፥ሴት የማህበረሰብ ስብራት የመሸከም አቅም አላት ፣ አለም ለሴቶች የትግል ሜዳ ናት ፣ እራስን መጠበቅ ፣ መማር ፣ መታገል ግድ ነው ሲሉ የህይወት ልምዳቸው በመጥቀስ አካፍለዋል።

የኢትዮጵያ ሴቶች የአለማቀፍ ታሪክ አምሳያ አላቸው ፥ በሀገሪቱ ያለው ለሴቶች የተሰጠው ቦታ ትልቅ ነው ፣ ከለውጡ በኋላ ለሴቶች ትልቅ እድል አለ ፣ ሴት እችላለሁ ካለች ትችላለች ብለዋል።

የግል ጥረት የአደባባይ ሽልማት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ የሴቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር በመርህ ደረጃ የተሰራ ስራ በተቋሙ መኖሩን በመጥቀስ በብዙ መንገድ እራስን መገንባት ያስፈልጋል ፣ የስራ ትጋት ላይ መጣር ግድ ነውና እቅድን አስፍቶ ማቀድ ፥ በሁሉም መስከ ለመረዳዳትና ለሀገራዊ ተልዕኮ ለመዘጋጀት በውስጥ መትጋት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የስልጠናው ተሳታፊዎች በተቋሙ ድፍረት የሚጠይቁ ውሳኔዎችን መስጠት ተችሏል ይህም በሴቶች መሪነት እና ተሳትፎ የመጣ ነው የለውጡ ቱሩፋት ማሳያ ጭምር ፥ለእኛም ህያው ምሳሌ ነው በማለት ከስልጠናው ብዙ እንደሚመሩ አንስተዋል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……

Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
https://www.ics.gov.et