ለተሟላ ለውጥ የስትራቴጂክ እቅዶች ዋጋቸው ትልቅ ነው – ቢቂላ መዝገቡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር

አዳማ ፣ መጋቢት ፣ 02 ፣ 2018 ዓ.ም
የቤተሰብ እና ሲቪል ምዝገባን ዲጂታላይዝ ማድረግ ላይ ያተኮረ ስልጠና በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።ስልጠናው ላይ በመገኘት የገመገሙት የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የዜግነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ቢቂላ መዝገቡ የቤተሰብ እና ሲቪል ምዝገባን ዲጂታላይዝ ማድረግ ለሀገር መሰረት መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም ተቋሙ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በመሆን ያለማው የቤተሰብና ሲቪል ምዝገባ ሲስተም ላይ በ አዳማ ከተማ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ተቋሙ የያዘውን እቅድ ለማሳካት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል። የቤተሰብና ሲቪል ምዝገባን በዲጂታል መልክ ለማከናወን ታስቦ የተሰራው ይህ ሲስተም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለማሳካት ጉልህ ድርሻ እንዳለው አውስተዋል።
በስልጠናው ላይ የተገኙት የአገልግሎቱ ሰራተኞች ስልጠናው ስራቸውን በላቀ ደረጃ ለማከናወን ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ከቴክኖሎጂ ስልጠናው ጎን ለጎን የተቋሙ የ3አመት ስትራቴጂክ እቅድ ጥናት በአዳማ ከተማ እየተከናወነ ይገኛል። በቦታው በመገኘት ሂደቱን የገመገሙት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቢቂላ ተቋሙ ላለፉት አመታት አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልፀው ለዚህም በእቅድና ጥናት መመራቱ ነው ብለዋል።

አቶ ቢቂላ አክለውም ተቋሙ የደህንነት ተቋም እንደመሆኑ በስትራቴጂክ እቅድ ስራው ላይ ይህን የተቋሙን ባህሪ በመረዳት መንቀሳቀስ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከ130 ሚልዮን ህዝብ በላይ አገልግሎት የሚሰጥ ትልቅ ሃላፊነት ያለበት ተቋም መሆኑን በመገንዘብ በእቅድ መመራት እና እስትራቴጂካዊ ንድፍ ማውጣት በሱም መመራት ዋጋው ትልቅ መሆኑን ጨምረው አንስተዋል ።

ስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ሁሉም ሰራተኛ በአግባቡ ሀላፊነቱን በመወጣት ተቋሙ እያከናወነ ያለውን ለውጥ በበለጠ ሁኔታ የማስቀጠል ሃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/