አገልግሎቱ አምስት ሚልዮን ብር ለመቄዶንያ ለገሰ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 05 ፣2018 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን የስራ እንቅስቃሴ በየ ክፍሉ በመዘዋወር ጎብኝተዋል ፥ የጉብኝቱ ዓላማ የማዕከሉን ተግባር ከመደገፍ ባሻገር ተገልጋዩን ለመደገፍ ያለመ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተገልጋዩን ፍላጎት ለማርካት ልዩ ልዩ የአገልግሎት አይነቶችን ከመቼውም ግዜ በላይ በላቀ አቀራረብ ፣ በቅርንጫፍ አድማስ ፣ በጥራት ፣ በዲጂታል አማራጭ በከፍተኛ የስራ ትጋት ወደ ህዝቡ እየደረሰ ይገኛል ያሉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት መቄዶንያን መጎብኘት ማህበራዊ ሃላፊነትን መወጣት መሆኑን አንስተዋል ።

አገልግሎቱ በህግ የተሰጠውን ሃላፊነት ከመወጣት ባሻገር በማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ በዚህ ልክ ማዕከሉ ለዜጎች ድጋፍ በመቆሙ ኢትዮጵያ ታመሰግናችዋለች ብለዋል።

በጉብኝቱ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለመቄዶንያ የአምስት ሚልዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ለማዕከሉ ተገልጋዮች የምሳ ግብዣም አድርጓል ፥ ስጦታው ከዋና ዳይሬክተሯ እና ከምክትል ዋና ዳይሬክተሮች የተቀበሉት የክቡር ዶክተር ቢንያም በለጠ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከዚህ ቀደም በበጎ ስራው እናውቀዋለን በማለት ለዛሬው ድጋፍም አመስግነዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም ለመቄዶንያ የሚደረገው የትኛውም ድጋፍ የሚመጥን አይደለም በማለት ተቋሙ የተቻለውን ሁሉ ከሰራተኞች በማሰባሰብ በቀጣይ ማዕከሉን ለመርዳት ዝግጁ መሆኑ አንስተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የተቋሙ ሰራተኞች ተገኝተዋል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !

————————

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……

Telegram: https://t.me/ICS_EthiopiaFacebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopiaTwitter: https://twitter.com/ics_ethiopiaTikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopiaLinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopiaYouTube: https://www.youtube.com/@Ics_EthiopiaInstagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/