ለኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የውጭ ዜጎች ቁጥጥርና ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

የተገልጋዮች/ደንበኞች አያያዝ፣ የውጭ ዜጎች ቁጥጥርና ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የሃሰተኛና የተጭበረበሩ ሰነዶች ልየታ ላይ ያተኮረ በስልጠናና ስርፀት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በአደማ ከተማ ካኔት ሆቴል ከግንቦት 10-11/2016 ዓ.ም መሰጠቱ  የተገለጸ።

በስልጠናው መክፈቻ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የዉጭ ዜጎች ቁጥጥርና ቆንስላ ጉዳዮች  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  አቶ ዲሪባ ባቡ ስልጠናው ተቋሙ የጀመረው የሪፎርም ሂደት የተቋሙ የሰው  ኃይል በአቅም መገንባት ቁልፍ አካል እንደሆነና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁ ሲሆን በተመሳሳይ  በተቋሙ የሚስተዋሉ የደምበኛ አያያዝ ክፍተት ከሞምላትና ሃሰተኛና የተጭበረበሩ ሰነዶች በመጠቀም በህገውጥ መንገድ አገር ውስጥ የሚንቀሳሱ የውጭ አገር ዜጎች በመቆጣጠርና ህጋዊ የውጭ ዜጎች እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ትልቅ ሚና እንደሚነረው ገልጿል።

በመጨረሻም ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙት አቅም ወደ ተግባር በመለወጥ ተቋሙ የጀመረው የለውጥና ሪፎሩም ትግበራ የበኩላችው እንዲወጡ አሳስቧል።

የስልጠናና ስርጸት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ከተማ አለሙ   እንደ ተቋም የሚነሱብንን የደንበኞች/ተገልጋዮች አያያዝ ውስንነቶች በአግባቡ በመረዳትና ትርጉም በመስጠት የሚስተካከሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጣችን እርካታ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የበኩላችንን አስተዋጾ መወጣት እንዳለብን ተነገሩ።

ስልጠናው የደምበኛ አያያዝ፣ የውጭ ዜጎችና ቆንስላ ጉዳዮች ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም ሃሰተኛና የተጭበረበሩ ሰነዶች ልየታ በሚሉ የስልጠና ሰነዶች ቀርበው  በመድረኩ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ስልጠናው ተጠናቋል።