በቅርቡ ተቋሙን ለተቀላቀሉ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ እና በጉዞ ሰነድ አያያዝ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።






ስልጠናውን የኢትዮጵያ አየርመንገድ እና አለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ከኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ጋር በትብብር ያዘጋጁት ነው።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እያካሄደ ያለውን ሁለንተናዊ የሪፎርም ስራ በብቁ የሰው ሀይል ዘርፍ ለመደገፍ እና ተቋሙ በቀጣይ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ የተቀላጣፋና የደንበኞቹን እርካታ ከፍ የሚያደርግ እንዲሆን በማለም ለሰራተኞቹ የተሰጠ መሆኑንም ተጠቁሟል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
