አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2018 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የዘርፍ እና የዳይሬክቶሬት የእቅድ ካስኬዲንግ ስነስርዓት አካሄደዋል፥የተሻለ እና የተናበበ ስራን በመስራት በእቅድ መመራት ለተሟላ አፈጻጸም የሚረዳ መሆኑም ተገልፆዋል ።
የስራ ክንውን እና የዘርፍ አፈፃፀምን ከተገልጋዩ ፍላጎት መሟላት ጋር አዛምዶ በመተንተን እና ስኬትን በመገምገም የአግልግሎቱን እቅድ የመፈፀም አቅም ማየት እንደሚገባ በካስኬዲንግ ስነስርዓት ላይ የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የዜግነት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ቢቂላ መዝገቡ መመሪያ ሰጥተዋል ።
በዲጂታል አሰራር የዘመን ስረአት በመገንባት ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት በአዲሱ በጀት አመት እንደሚሰጥም አንስተዋል።
የአለምን ነባራዊ ሁኔታዎች በመገንዘብ ለሚመጡ የስራ ላይ ተግዳሮቶች ከእቅድ ጋራ የተጣጣሙ የመፍትሔ ሃሳቦችን በማመንጨት ለስራ ስኬት መትጋት እንደሚገባ የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የኢሚግሬሽን ዘርፍ ሃላፊ ኢንጅነር ጎሳ ደምሴ አስገንዝበዋል ።
ህዝብን በማገልገል ሂደት እና በተሻለ የስራ ተነሳሽነት እቅድን መተግበር እንደሚገባም ተናግረዋል ።
በዜግነት ዘርፍ የፓስፖርት አገልግሎት ፣ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፣ በኢሚግሬሽንና ዘርፍ ደሞ የብስ እና አየር ድንብር አስተዳደር ፣ የውጪ ዜጎች ቁጥጥር እና አገልግሎት
ዳይሬክቶሬቶች በስነስርዓቱ ላይ በመገኘት የህዝብ እና የመንግስትን ሃላፊነት በአግባቡ በተሻለ የስራ ስኬት ለመከወን እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
