ደም በመለገስ በደም እጦት ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎቻችንን እንታደጋለን-የአገልግሎቱ ሰራተኞች

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 23 ፣ 2018 ዓ.ም  “እያንዳንዱ ደም ለጋሽ ህይወት አዳኝ ነው” በሚል መሪ-ሃሳብ  የደም ልገሳ መርሃ ግብር የዋናው መስሪያ ቤት የተለያዩ የስራ ክፍሎች ሰራተኞች እና ሃላፊዎች በተገኙበት ተጀመረ ።

የደም ልገሳውን መርሃግብር የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የዜግነት ዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለ ሽፈራው በማስጀመር ፥ አገልግሎቱ በተከታታይ አመታት  የደም ልገሳ መርሃ ግብር  እያከናወነ መሆኑን በመግለፅ ከአገልግሎት ባሻገር ማህበራዊ ሃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል ።

ይህ በጎ ተግባር ከአመት አመት እየተሻሻለና እየዳበረ መሆኑን ገልፀው ለጋሾች የዛሬው በጎ ተግባር ህይወት ማዳን መሆኑን በመረዳት በዚህ መልኩ መሳተፋቸው የሚደነቅ ነው ብለዋል ።

በኢትዮጵያ ደምና ህበረ-ህዋስ  ባንክ አገልግሎት ትምህረትና ቅስቀሳ ላይ የሚሰሩት ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ ማንኛውም ሰው በየሶስት ወሩ ደም መለገስ እንደሚችል ገልፀው፥ደም በመለገሳችን የአንድ ሰው ህይወት እንድንታደግ ያስችለናል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በየአመቱ የተቋሙን ሰራተኞች በማስተባበር ለሚያደርገው የደም ልገሳ ምስጋናቸውንም  አቅርበዋል።

በመርሃግብሩ የተሳተፉ የተቋሙ ሰራተኞች ከአገልግሎት ባሻገር የማህበራዊ ተሳትፎ አካል በሆነው የደም ልገሳ መርሃ ግብር  ላይ መሳተፋችን ህይወታቸውን በደም እጦት የሚያጡ ዜጎቻችንን እንድንታደግ ያስችለናል ሲሉም ተናግረዋል ፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/