በኢትዮጵያ የሲቪል ምዝገባ ስርዓትን ዲጅታላይዝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

በመላ ሀገሪቱ የሲቪል ምዝገባን ወጥ ለማድረግ የቴክኖሎጅ ስራዎች  እየተሰሩ መሆኑን የኢሚግሬሽንና  ዜግነት አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ተስፋየ ወልዴ አስታውቀዋል።

በዋና ዳይሬክተር  አማካሪ የተመራ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች  ልዑክ የኢትዮጵያ  የሲቪል ምዝገባና ስታትስቲክስ መረጃ  ላይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በናሚቢያ  ዊንድሆክ ይገኛል። 

የናሚቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ የኢሚግሬሽና ደህንነት ሚኒስትር ሉሲያ ኢፑምቡ  የልዑካን ቡድኑን በቢሯቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን እንደ አህጉር እጅ ለእጅ ተያይዘን የሲቪል ምዝገባን እና ሌሎች ግቦቻችንን ተግባራዊ ለማድረግ በጋራ  መስራት አለብን ብለዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ምዝገባውን ከማንዋል /ወረቀት/ ወደ ዲጂታል መመዝገቢያ ሥርዓት ለማሸጋገር እና ለማዘመን ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል ያሉት የዋና ዳይሬክተር አማካሪው በሀገር አቀፍ ደረጃ የተደረገውን ግምገማ ተከትሎ የአምስት አመት የCRVS ስትራቴጂክ እቅድ የተዘጋጀ ሲሆን በዚህ ረገድ የሲቪል ምዝገባ ሥርዓትን ዲጂታይዝ በማድረግ ላይ አስደናቂ እድገት ያስመዘገበች አገርን  የስኬት ተሞክሮዎች መማር  ለእኛ ጠቃሚ ነው ብለዋል።

አክለውም  የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የዲጂታል ሲቪል ምዝገባ እና የማንነት ስርዓቶችን በማስተዳደር ረገድ ስኬታማ ስልቶችን ለመውሰድ እንደሆነ  በመግለፅ ለፈጣን ምላሻቸውና ለተደረገላቸው አቀባበል በተቋሙ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ። 

ናሚቢያ በዘርፉ ያላትን ምርጥ ተሞክሮ ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና አተገባበር ላይ ያስመዘገበችውን ስኬት፣ ያጋጠማትን ተግዳሮትና ፈተናዎችን የተወጣችበት መንገድ በሚመለከት ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

ልዑኩ የከተማና የገጠር የሲቪል መመዝገቢያ ጽ/ቤቶችን፣ የካቱታራ ግዛት ሆስፒታል ፣ የዊንድሆክ ፖሊስ እና የናሚቢያ ፖሊስ ፎረንሲክ ላብራቶሪን ጎብኝቷዋል።

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133