ኢትዮጵያ እና ቱርክ የፍልሰት ትብብርን ለማጎልበት ያለመ የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ።

የኢሚግሬሽንና  ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ የቱርክ መንግስት የፍልሰት አስተዳደር የሉዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን በአገልግሎት መ/ቤቱ የፍልሰት ፓሊሲዎች፣ የአሰራር ማዕቀፎች እና የድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር መኖሩን ገልፀው አሁን ላይ  እያጋጠሙ ያሉ  ተግዳሮቶችን በዝርዝር አስረድተዋል::

በውይይቱ  የሁለትዮሽ የትብብር ጥረቶችን ለማጎልበት፣ ከስደት ተመላሾች ጋር እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎችን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን ለመስራት ፣ ተቋማዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እና በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ተገልፆል።

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133