አዲስ አበባ: ሀምሌ 8/2017 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች እና አመራሮች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጭ እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ዲማ ነገዎን ጨምሮ በ2017 እቅድ አፈፃፀም እና 2018ዓ.ም. እቅድ ጉባኤ ላይ የተሳተፉ የፌድራል፣ የክልል መዝጋቢ እና ባለድርሻ አካላት ጎተራ ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፊት ለፊት በሚገኘዉ የብሄር ብሄረሰቦች ማሳለጫ የችግኝ ተከላ አከናዉነዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ለህብረተሰቡ ከሚሰጠዉ አገልግሎት በተጨማሪ በአርንጓዴ አሻራ እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ሃገራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለዉ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ለሃገር ትልቅ አስተዋጾ እንዳለዉ የገለጹት ዳይሬክተሯ ችግኞችን መትከል ከአረንጓዴ አሻራና አየር ንብረት ሚዛን ከመጠበቅ በተጨማሪ አገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል ለምታደርገው እንቅስቃሴ የራሱ አወንታዊ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
አክለውም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአንድ ቀን ሥራ ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት እና በቅንጅት ሊሠራ የሚገባው በመሆኑ በቀጣይም የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
