የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ያሳየዉን የላቀ አፈጻጸም በቀጣይ አመትም አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅትን የገመገመበት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም በሪፎርም ሥራዎች አፈፃፀም የታዩትን ጠንካራ ጎኖችና የገጠሙትን ተግዳሮቶች በጥልቀት ተዳሰዋል።

በተጨማሪም በበጀት አመቱ የታዩ አመርቂ አፈፃፀሞች የተበረታቱ ሲሆን፣ የተለዩ ክፍተቶችን ደግሞ በቀጣዩ 2018 በጀት ዓመት ለማሻሻል የሚያስችሉ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ያሳየዉን የላቀ አፈጻጸም በቀጣይ አመትም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተነግሯል። 

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133