በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለተቀጠሩ አዲስ ባለሙያዎች በአቬሽን ዩኒቨርሲቲ ስልጠና እየተሠጠ መሆኑ ተገለፀ።

ግንቦት 20/2017 ዓ.ም

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በቅርቡ ለተቀላቀሉ 280 አዲስ ባለሙያዎች በአቬሽን ዩኒቨርሲቲ ለ4 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየተሠጠ መሆኑ ተገልፆል።

የተቋሙ  የአየር ድንበር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ወንድሙ  ቀደም ሲል በአፍሪካ አመራር አካዳሚ እንዲሁም በኢትዮጵያ ስታስቲክስ ማእከል ስልጠናወች የተሠጡ መሆኑን ገልፀው ባለሙያዎቹ የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያደርጉ ስልጠናወችን ለመስጠት ከሚችሉ ተቋማት ጋር አብሮ በመሥራት የበቃና የነቃ ባለሙያን ለማፍራት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል ብለዋል።

አክለውም ስልጠናው የሀገራችን ብሎም የአፍሪካ ኩራት የሆነውን አየር መንገድ በሚመሩና ብቃት ባላቸው አሠልጣኞች እየተሠጠ እንደሆነ ጠቅሰው እንደተቋም የተሠጠን ሃላፊነት ከመወጣት ባለፈ የደንበኛ አያያዝ፣ የላቀ አገልጋይነት እና ከአየር መንገድና ከአቬሽን ጋር የተያያዙ ስልጠናዎች እየተሠጡ መሆኑን ተናግረዋል። 

በመጨረሻም አስፈላጊውን ግብዓት ሁሉ በማሟላት ይህንን ስልጠና እየሰጠ ለሚገኘው ለአየር መንገድ አመራሮችና አሠልጣኞች ምስጋና አቅርበዋል።

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133