የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት ከነበረው የኦንላይን አፕሊኬሽን በተጨማሪ በቅርቡ በጀመረው የኢ-ፓስፖርት የኦንላይን አፕሊኬሽን https://www.immigration.gov.et በመጠቀም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን:-
በአዲሱ ሲስተም የምንሰጠው አገልግሎት
– አስቸኳይ አዲስ፣ እድሳት፣ የጠፋ፣ የተበላሸ እንዲሁም እርማት ሲሆን በቀጠሮ ቀናችሁ ጎተራ በሚገኘው ኢሚግሬሽን ቢሮ እንዲሁም በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአካል በመገኘት መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ:- ወደተቋማችን ሲመጡ የፋይዳ መታወቂያ እና ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
