የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባሉት ክፍት የስራ መደቦች ብቁ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር ከዚህ ቀደም ምዝገባ ማከናወኑ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም መጋቢት 13 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በሁሉም ክልሎች ዋና ከተማ ፈተና የሚሰጥ ስለሆነ ለፅሁፍ ፈተና ያለፋችሁ ስም ዝርዝራችሁን ከዚህ በታች የገለጽን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ጥብቅ ማሳሰቢያ፡-
- ለፈተና የተመረጠው በመጀመሪያ ዲግሪ የተመዘገቡትን ሲሆን በዲፕሎማና በሌብል የተመዘገባችሁ ወደፊት የምናሳውቅ ይሆናል።
- ፈተናው ጠዋት 2:30 ከሰአት 7:30 የሚጀምር ሲሆን በሰአቱ የአልተገኘ ተፈታኝ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
- ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል።
- ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ /ስልክ / ይዞ መግባት አይፈቀድም
- የስም ዝርዝራችሁ ካለበት ቦታ ውጭ ቦታ ቀይሮ መፈተን አይቻልም።
